በጣና ሐይቅ ላይ የተንሠራፋውን የእንቦጭ አረም በዘላቂነት ለማስወገድ እየሠራ መሆኑን የጣና ሐይቅና ሌሎች የውኃ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ አስታወቀ።

98
ነጭመደበኛ
ነጭመደበኛ

ባሕር ዳር: መጋቢት 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የጣና ሐይቅና ሌሎች የውኃ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ ሥራ አስኪያጅ አያሌው ወንዴ (ዶክተር) ለአሚኮ እንደገለጹት የጣና ሐይቅ በእንቦጭ አረም ከተወረረ ወዲህ በሐይቁ ብዝኃ ህይወት ላይ ከፍተኛ ችግር አሰከትሏል። ችግሩን ለመፍታትም ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ የተለያዩ ተግባራት ሲከናወኑ ቆይተዋል ብለዋል።

ዶክተር አያሌው እንዳሉት:–

👉በ2013 ዓ.ም መስከረም ወር ላይ በሐይቁ ላይ በተለይ በሊቦ ከምከምና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች ተንሰራፍቶ የነበረውን 5 ሺህ ሄክታር የእንቦጭ አረም ለማስወገድ ከማሽን ሥራ ባለፈ 400 ሺህ የሰው ኀይል ተሳትፎአል።

👉በዚህ ወቅት ጨርሶ አረሙን ለማስወገድ የተያዘው እቅድ እንዳይሳካ የበጀትና ወቅታዊ የክልሉ ሁኔታ ፈተና ነበር።

👉በ2014 ዓ.ም መስከረም ወር በተደረገው ጥናትም 2 ሺህ 800 ሄክታር የእንቦጭ አረም በ30 ቀበሌዎች ተንሰራፍቶ በመገኘቱ አረሙን ለማስወገድ እየተሠራ ይገኛል።

👉በዚህም በተጠቀሱት ቀበሌዎች በቀን ከ200 በላይ የሰው ኀይል (አርሶ አደሮች)፣ አረሙ በተንሰራፋባቸው 4 ቀበሌዎች (ልምባ፣ ሸሃ፣ ፍርቃ፣ ምጥረሃ) ደግሞ ከሰው ኀይል በተጨማሪ አምስት ማሽኖች የማስወገዱን ሥራ እያከናወኑ ነው።

👉አሁን ላይ ባለው አፈጻጸምም አብዛኛዎቹ ቀበሌዎች እስከ ሚያዚያ 30 የማስወገድ ሥራውን እንደሚያጠናቅቁ ታውቋል።

👉በሥራው ሂደት እያጋጠመ ያለውን የሕክምና እና የንጽሕና መጠበቂያ ችግር ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ኀላፊው አመላክተዋል።

👉የጣና ሐይቅን የእንቦጭ አረም በዘላቂነት ለማስወገድ በሐይቁ ዳርቻ እንደ ደንገል፣ ፊላ፣ ሳርና ሌሎች እጽዋትን መትከል ያስፈልጋል። ለዚህ ደግሞ የሐይቁ ወሰን በሕግ ማዕቀፍ ሊከበር ይገባል፣ ኤጀንሲውም የሕግ ማዕቀፉን በማዘጋጀት ለማጸደቅ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ዘጋቢ:–መላኩ ሙሉጌታ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/