በጎንደር ከተማ የንፁሕ መጠጥ ውኃ ተበክሏል እየተባለ በማኅበራዊ ገጾች የተለቀቀው መረጃ የተሳሳተ መሆኑ ተገለፀ።

206

ባሕር ዳር፡ መስከረም 22/2012 ዓ/ም (አብመድ) የጎንደር ከተማ አስተዳደር ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽሕፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነትና የደንበኛች አገልግሎት ቡድን መሪ አቶ አወቀ አሰፈሬ እንደገለፁት በሁሉም የውኃ ታንከሮች የጥበቃ አገልግሎት ስላለ ውኃው የሚበከልበት አጋጣሚ የለም። ከዚህም በተጨማሪ ውኃው በላብራቶሪ እየተመረመረ ወደ ኅብረተሰቡ የሚሰራጭ ስለሆነ የጎንደር ከተማ ሕዝብ በአሉቧልታው ሳይደናገጥ የውኃ አቅርቦቱን መጠቀም እንደሚችል ነው የተናገሩት።

በዚህ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን የምናቀርብ ይሆናል፡፡