በድጋሜ በኮሮናቫይረስ የተያዘው ሰውየ ከመጀመሪያው የከፋ ሕመም አጋጥሞታል፡፡

0
138

ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 03/2013ዓ.ም (አብመድ) በአሜሪካ ከዚህ ቀደም በኮሮናቫይረስ ተይዞ የነበረ ሰው በድጋሜ መያዙንና የሕመሙ ሁኔታ ከመጀመሪያው የከፋ መሆኑን የሕክምና ባለሙያዎች አስታወቁ፡፡

የ25 ዓመቱ ወጣት በሁለተኛው ዙር ሕመሙ ሳምባው ክፉኛ በመጎዳቱ ሆስፒታል ገብቶ አጋዥ መተንፈሻ እንደተገጠመለት ታውቋል፡፡

በቫይረስ በሚመጡ በሽታዎች ደግሞ የመያዝ ዕድል አነስተኛ እንደሆነና ቢይዝም ሕመሙ ቀለል ያለ እንደሆነ ሲገለጽ የነበረ ቢሆንም አሁን በዚህ ግለሰብ ላይ የታየው የጠየና ባሙያዎችን ያነጋገረ ጉዳይ ሆኗል፡፡

ላንሴት የተላላፊ በሺታዎች ጥናት ማዕከል ምን ያህል የመከላከል አቅም ሲዳብር ቫይረሱን መቋም እንደሚቻል መጠየቅ ጀምሯል፡፡
በአሜሪካ ናቫዳ ነዋሪው ግለሰብ በቫይረሱ እንዲጠቃ የሚያደርግ የተለዬ የበሽታ መከላከል አቅም ውስንነት የሌለበትና የጤና ችግር ያልነበረበት እንደሆነ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ብዙ ሰዎች የኮሮናቫይረስ አንድ ጊዜ ከያዘ መልሶ የማይይዝ ይመስላቸዋል፤ በአሜሪካ ያጋጠመው ግን የበለጠ ሕመም የሚያስከትል ሆኖ ድጋሜ ሊይዝ እንደሚችል ያረጋገጠ ነው፡፡ ስለዚህ ያልተያዙም ሆነ ተይዘው ያገገሙ ሰዎች እኩል መጠንቀቅ ይኖርባቸዋል ማለት ነው፡፡

በአብርሃም በዕውቀት