“በደግነታቸውና ወደር በሌለው አዛኝነታቸው የሚታወቁት የአበበች ጎበናን ዜና ረፍት በከፍተኛ ሐዘን ነው የስማሁት” ፕሬዝዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ

0
35

“በደግነታቸውና ወደር በሌለው አዛኝነታቸው የሚታወቁት የአበበች ጎበናን ዜና ረፍት በከፍተኛ ሐዘን ነው የስማሁት” ፕሬዝዳንት
ሣኅለወርቅ ዘውዴ
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 27/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ፕሬዝዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ የክብርት ዶክተር አበበች ጎበና ሕልፈተ ሕይወት
አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
“በደግነታቸውና ወደር በሌለው አዛኝነታቸው የሚታወቁት የአበበች ጎበናን ዜና ረፍት በከፍተኛ ሐዘን ነው የስማሁት” ብለዋል፡፡
“አበበች ጎበና የራሳቸው ልጅ ባይኖራቸውም በርካታዎችን እንደ ራሳቸው ልጆች አሳድገዋል፡፡ ከ1977 ድርቅ ሁለት ልጆችን
በማሳደግ በጀመሩት የበጎ አድራጎት የተቀደሰ ተግባር ባለፉት 36 አመታት በርካታ ኢትዮጵያዊያንን አሳድገው ለቁም ነገር
አብቅተዋል” ነው ያሉት፡፡
ከክብርት ዶክተር አበበች ጎበና ተግባር መማር እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ለክብርት ዶክተር አበበች ጎበና ቤተሰቦች፣ ዘመዶችና ወዳጆች መጽናናትን መመኘታቸውን
ከጽሕፈት ቤታቸው የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here