በውጭ ጉዳይ ፖሊሲያችን ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያለንን አጋርነት ማጠናከር ቀዳሚ ትኩረታችን ነው…ሰርጌይ ላቭሮቭ

0
70
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 17/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በሩሲያ ውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ቅድሚያ ከምንሰጣቸው ቁልፍ ጉዳዮች አንዱ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያለንን ሁሉን አቀፍ አጋርነት ማጠናከር ነው ሲሉ የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ አስታወቁ።
ሚኒስትሩ የሀገሪቱን ቀጣይ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲና ስትራቴጂ በተመለከተ በሰጡት መግለጫ “ቅድሚያ ሰጥተን ከምንሰራባቸው የውጭ ጉዳይ ቁልፍ ስራዎች መካከል ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያለንን ሁሉን አቀፍ አጋርነት ማጠናከር ነው” ብለዋል።
እ.አ.አ በ2019 ስትራቴጂካዊ በሆነ ውሳኔ በሶቺ የተጀመረው የሩስያ አፍሪካ ጉባኤ የሁለትዮሽ ግንኙነቱን የበለጠ ለማጠናከር የሚያስችል ሲሆን ሩሲያም ይህንን ለማሳደግ ትሰራለች ነው ያሉት።
በአለም አቀፉ መድረክም የአፍሪካውያን ድምጽ እንዲሰማ እንፈልጋለን ፤ በተለይ በአሁኑ ወቅት ለአለም ምጣኔ ሀብት ስኬት የአፍሪካ ሀገራት ሚና ከፍተኛ ነው ሲሉ አንስተዋል።
ለዚህም ባለፉት አስርት አመታት የአፍሪካ ሀገራት የሀገር ውስጥ ምርት 50 በመቶ ማደጉ ግልጽ ማሳያ ነው ብለዋል ላቭሮቭ በመልዕክታቸው።
ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አክለውም የሩስያና የአፍሪካ ግንኙት ወንድማማችነትን ባጠናከረና ሉዓላዊነትን ባከበረ መልኩ ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን ከኤምባሲው ድረ-ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ለሀገር ክብር በትግል እናብር!!