በወልድያ ከተማ ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኀይል በድጋሚ ወደ አገልግሎት ተመለሰ፡፡

0
50

ወልድያ፡ ጥር 07/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በወልድያ ከተማ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኀይል አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡ ጉዳት የደረሰባቸውን የዲስትሪቢውሽን ትራንስፎርመሮች በመቀየር፣ የተሰረቁ ትራንስፎርመሮችን እና ሌሎች ግብዓቶችን በመተካት የኤሌክትሪክ አገልግሎቱ እንዲጀምር መደረጉን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኀይል የከፍተኛ ኤሌክትሪክ መስመር ጥገና ኀላፊ አቶ ተስፋየ መንግሥቱ ተናግረዋል።

አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ወልድያ ከተማን ጨምሮ በዞኑ ባሉ ከተሞች የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ ያደረሰው ጉዳት እና ውድመት ከፍተኛ ቢሆንም በተቋሙ የሥራ ኀላፊዎች እና በሠራተኞቹ ከፍተኛ ርብርብ ወደ ሥራ ማስገባት መቻሉን ኀላፊው ገልጸዋል።

በቀጣይም ሌሎች አካባቢዎችን አገልግሎት እንዲያገኙ ለማስቻል እየተሠራ መሆኑንም ኀላፊው ጠቁመዋል።

ዘጋቢ፡-ባለ ዓለምየ-ከወልድያ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ። https://ameco.bankofabyssinia.com/