በኹለት ሳምንታት ውስጥ ከ41 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ከሳውዲ አረቢያ መመለስ መቻሉን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ።

0
36

በኹለት ሳምንታት ውስጥ ከ41 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ከሳውዲ አረቢያ መመለስ መቻሉን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ።

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 22/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የሰላም ሚኒስቴር የሕግ ማስከበር ዳይሬክተር አቶ አምባዬ ወልዴ በሳውዲ አረቢያ በከፋ እንግልት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ለማስመለስ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።

ግብረ ኃይሉ ባከናወነው ተግባርም ከሳውዲ አረቢያ በኹለት ሳምንታት ብቻ 41 ሺህ 400 ዜጎች መመለስ ተችሏል ብለዋል ዳይሬክተሩ። በቀን ከ1 ሺህ 500 እስከ 3 ሺህ ዜጎች አቀባበል እየተደረገላቸው መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡

አቶ አምባዬ እንደገለጹት ከተመላሾቹ 2 ሺህ 401 ጨቅላ ሕጻናት ይገኙበታል። ከሲዳማ ክልል ውጭ በሁሉም ክልሎች በርካታ ተመላሾች በቁጥሩ የተካተቱ ሲሆን ከመጡት 13 ሺህ 912 ከትግራይ፣ 13 ሺህ 813 ከአማራ እና ቀሪዎቹ ከሌሎች ክልሎች ናቸው ተብሏል።

ለተመላሾቹ በቂ የሥራ ዕድል መፍጠር እንደሚገባ እና ለዚህም ከሚመለከታቸው የክልል የሥራ ኀላፊዎች ጋር ውይይት እንደሚደረግ አቶ አምባዬ አስታውቀዋል፡፡

በሳውዲ አሁንም በርካታ ዜጎች በስቃይ ውስጥ እንደሚገኙ እና ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።

ዜጎች እንዲሰደዱ የሚያደርጉ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን፣ የአሠራር ብልሹነት እና መሰል በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን ገፊ ምክንያቶች ለመቅረፍ በርካታ ሥራዎች መሠራት እንዳለበት ዳይሬክተሩ በመግለጫቸው አንስተዋል።

ዘጋቢ፡- አንዱዓለም መናን-ከአዲስ አበባ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here