በኮርያ መንግሥት ድጋፍ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ማበልፀጊያ ማዕከል ሊቋቋም ነው።

96

መጋቢት 17/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የኮርያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ በአይሲቲ ፓርክ ውስጥ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራ ማበልፀጊያ ማዕከል ግንባታና ድጋፍ ዙሪያ መክረዋል።

ማዕከሉ በኮርያ መንግሥት ድጋፍ በ600 ሺህ ዶላር ወጪ በአይ ሲ ቲ ፓርክ ውስጥ የሚገነባ ሲኾን የቴክኖሎጂ ፈጠራ ባለቤቶች የፈጠራ ሥራዎቻቸውን የሚያበለፅጉበትና ወደ ንግድ የሚለውጡበት ነው።

በኮርያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ ድጋፍ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እስከ 2025 የሚቆይ የ10 ሚሊየን ዶላር ፕሮጀክት ተቀርፆ እየተተገበረ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ (ዶ.ር) በዚህ ፕሮጀክት እየተደገፉ ያሉና ተወዳድረው ለተመረጡ 10 ጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች እስከ 5 ሺህ ዶላር የሚደርስ የመነሻ ገንዘብ ተሰጥቷቸው በቅርቡ ይመረቃሉ ብለዋል።

የቴክኖሎጂ የፈጠራ ሥራ ያላቸው ዜጎች በቀላሉ ብድር የሚያገኙበት ሁኔታ ላይ እየተሠራ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው የኮርያ መንግሤት እያደረገው ላለው ድጋፍ ምሥጋናቸውን አቅርበዋል።

የኮይካ የኢትዮጵያ ምክትል ተወካይ ሺንያንግ ሊ የኮርያ መንግሥት በኢትዮጵያ የፈጠራ ሥራ እንዲዳብር ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ መግለጻቸውን
ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

የዲዛይን ሥራው የተጠናቀቀው ማዕከሉ በአይ ሲ ቲ ፓርክ ውስጥ የሚቋቋም ሲኾን የውስጥ እድሳት ሥራ፣ የፈጠራ የንድፍ ሥራ መሳሪያዎች፣ ባለሙያዎች እና አስፈላጊ መሳሪያዎች ይሟሉለታል ተብሏል።

ከልማት ባንክ እና ከተባበሩት መንግሥታት ልማት ድርጅት ጋር በጋራ በተዘጋጀው የጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች የብድር ዋስትና ላይ የመከሩ ሲኾን በተባበሩት መንግሥታት የኢኖቬሽን ልማት ፕሮጀክት ማዕቀፍ ላይ ትኩረት እንዲሰጠው አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ ‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/