በካርቱም ሰላም የአማራ መረዳጃ ማኅበር ራሱን በማጠናከር በሀገር ቤት የተሻለ በጎ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አስታወቀ።

0
125

ባሕር ዳር: የካቲት 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በሱዳን ካርቱም የሚገኘው ሰላም የአማራ መረዳጃ ማኅበር የተመሰረተበትን አንደኛ ዓመት አክብሯል።
የማኅበሩ ሰብሳቢ ወይዘሮ ቦሰና ዓለሙ ማኅበሩ የተቋቋመበትን ዓላማና በዓመቱ የሠራቸውን ሥራዎች በተመለከተ ማብራሪያ ሠጥተዋል፡፡ ማኅበሩ ሲጀመር በጥቂት እናቶች ቢሆንም አሁን ላይ የአባላቱ ቁጥር መጨመሩን ተናግረዋል፡፡
“ዛሬም ለወገኔ፤ ነገም ለኔ!” በሚል መሪ ሃሳብ በሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ቡድን ወረራ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች እና ለፀጥታ ኀይሉ በገንዘብ እና በዓይነት ድጋፍ ማድረጉንም ገልፀዋል።
ሰላም መረዳጃ አማራ ማኅበር በሰቲት ሁመራ በጦርነቱ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች፣ በማይካድራ በሽብር ቡድኑ ወላጆቻቸውን በሞት ላጡ ሕፃናት እና በደባርቅ ለፀጥታ አባላት ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ እንዳደረገ ወይዘሮ ቦሰና ጠቅሰዋል፡፡


በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሀገራዊ ጉዳይ ያደረገውን ጥሪ ተከትሎም መኅበሩ ድጋፍ ማድረጉን አንስተዋል፡፡
በቀጣይም የማኀበሩን አቅም በማጠናከር ለአባላቱ እና ለሀገር አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ይደረጋል ተብሏል፡፡
ማኅበሩ አንደኛ ዓመቱን ሲያከብር በሱዳን የኢፌዴሪ ኤምባሲ የሥራ ኀላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መታደማቸውን ከኤምባሲው ድረ ገፅ እና ከማኅበሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/