በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የስኬት ማዕከላት የማጎልበቻ ሥልቶችን ለመንደፍ ሀገር አቀፍ ጉባዔ በባሕር ዳር ከተማ መካሄድ ጀመረ።

16

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 18/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከኢፌዲሪ ሥራና ፈጠራ ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የስኬት ማዕከላት የማጎልበቻ ሥልቶችን ለመንደፍ ሀገር አቀፍ ጉባዔ በባሕር ዳር ከተማ ማካሄድ ጀምሯል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የሚያካሂዱት ይህ ጉባዔ በሥራና ክህሎት ማበልጸጊያና በሥራ እድል ፈጠራ ዙሪያ ሁሉም የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ የልማት አጋር ድርጅቶች፣ ቀጣሪ መሥሪያቤቶች ፣ የፋይናንስ ተቋማት የተገኙበት ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!