በእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ 15ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ማንቸስተር ዩናይትድ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል፡፡

0
202

ባሕር ዳር፡ ሕዳር 25/2012ዓ.ም (አብመድ) የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ 15ኛ ሳምንት ስድስት ጨዋታዎች ተካሂደዋል፤ በዕለቱ ተጠባቂ የነበረው የማቸስተር ዩናይትድና ቶተንሀም ሆትስርስ ጨዋታ በዩናይትድ 2ለ1 አሸናፊነት ተጠናቅቋል፡፡

ከዩናይትድ ከተሰናበቱ ከዓመት በኋላ ተቃራኒ ቡድን እየመሩ ወደ ኦልድትራፎርድ ያመሩት ጆዜ ሞሪኒሆ በድል እንደሚመለሱ ተገምቶ ነበር፡፡ ነገር ግን ተመጣጣኝ ጨዋታ ታይቶበት በባለሜዳው አሸናፊነት ተጠናቅቋል፡፡ እኩል የኳስ ቁጥጥር በታዬበት ጨዋታ ማንቸስተር ዩናይትዶች 6 ቶተንሀሞች 5 ዒላማቸውን የጠበቁ የግብ ሙከራዎችን አድርገዋል፡፡

የማንቸሸስተርን የማሸነፊያ ግቦች ማርከስ ራሽፎርድ በ6ኛውና 49ኛው ደቂቃ በጨዋታና በፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥሯል፤ የቶተንሀም ብቸኛ ግብ የተቆጠረቸው በዴሊ አሊ አማካኝነት በ39ኛው ደቂቃ ነው፡፡
ሞሪኒሆ ወደ ቀድሞ ቡድናቸው ሜዳ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል እንደተደረገላቸው ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ከጨዋታው በኋላ የዩማይትዱ አለቃ ኦሊጎናር ሶልሻዬር አጥቂያቸውን ራሽፎርድንና ማክተቶሚናይን አሞካሽተዋል፡፡ ድሉን ተከትሎም ዩናይትድ ወደ 6ኛ ደረጃ አድጓል፡፡

በሌሎች ጨዋታዎች ቸልሲ አስቶንቪላን እና ሳውዛምተን ኖርዊችን በተመሳሳይ 2ለ1 እንዲሁም ሌሲስተር ሲቲ ዋትፎርድን እና ወልቭስ ዌስትሀምን በተመሳሳይ 2ለ0 አሸንፈዋል፡፡ የሊጉ መሪ ሊቨርፑልም 5ለ2 በሆነ ውጤት ኤቨርተንን አሸንፎ ከተከታዩ ያለውን ልዩነት አስጠብቋል፡፡ ትናንት የነበሩ ስድስት ጨዋታዎችን ባለሜዳዎቹ አሸንፈዋል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ