በእስራኤል ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን ለህልውና ዘመቻው የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታወቁ፡፡

0
91

በእስራኤል ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን ለህልውና ዘመቻው የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታወቁ፡፡

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 29/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በእስራኤል ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን በድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴአቸው አማካኝነት ለአማራ ክልል የድጋፍ አሰባሳቢ ግብረ ኀይል በላኩት መልዕክት “እኛ እስራኤል ሀገር የምንኖር ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን እና ኢትዮጵያዊያን በአሸባሪው ትህነግ የተቃጣውን ጦርነት ለመደምሰስ ለመከላከያ ሠራዊት፣ ለልዩ ኀይልና ለሚሊሻ፣ ፋኖ እንዲሁም ከሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች ሕግ ለማስከበር እና የሕዝብን ህይወት ከጥቃት ለመከላከል ለተሰማራዉ የጸጥታ ኀይል የሚዉል ድጋፍ በማሰባሰብ ላይ እንገኛለን” ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያዊያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን አሸባሪው ትህነግ የፈጸመው ወረራ በእኛም ላይ የተቃጣ መሆኑን ተረድተን የአቅማችንን ገንዘብ በማሰባሰብ ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡ በዚህም 8 ሺህ ዶላር በማሰባሰብ መላካቸውን የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አስተባባሪ አምላኬ ዘለቀ ገልጸዋል፡፡

አሁንም በማሰባሰብ ላይ መሆናቸውን በመግለጽም እንዴት አሸባሪው ትህነግ ያጎረሰዉን ሕዝብ ለመዉጋት ይነሳል በማለት በቁጭት በመነሳሳት በድጋፉ በመሳተፍ ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡ መረጃውን ያደረሰን በእስራኤል ሀገር የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴው ነው፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here