በኢ.ፌ.ዴ.ሪ አየር ኃይል በማዕከላዊ አየር ምድብ የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ እና በሥራ አፈፃፀማቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የሠራዊት አባላት የማዕረግ ሹመት ተሰጠ።

0
98

የካቲት 21/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የማዕከላዊ አየር ምድብ አዛዥ ኮሎኔል ወንዱ ኬዳ በአሸባሪው ሕወሓት ቡድን በተካድንበት ወቅት ችግሮችን አልፋችሁ የላቀ የሥራ ውጤት በማስመዝገብ ለማዕረግ ሹመት በመብቃታችሁ ልትኮሩ ይገባል ብለዋል፡፡ የማዕረግ ሹመት ትልቅ አደራና ድርብ ኃላፊነት መኾኑን በመገንዘብ አኩሪ ድል ለማስመዝገብ በቁርጠኝነት በመሥራት ኃላፊነታችሁን ልትወጡ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

የተጀመሩ ሥራዎች አላለቁም፤ ጦርነቱም አልተጠናቀቀም ያሉት ኮሎኔል ወንዱ በምድቡ የሚገኙ የሠራዊት አባላትና ሲቪል ሠራተኞች አንድ ላይ በመኾን የተጀመረውን ተቋማዊ ለውጥ በማስቀጠል ከምንግዜውም በላይ በትጋትና በወኔ የቆማችሁለትን ዓላማ ለማሳካት ጠንክራችሁ መገኘት አለባችሁ ብለዋል፡፡

የምድቡ ምክትል አዛዥ ለሰው ኃብት ልማት ኮሎኔል ወርቁ ፈረደ በበኩላቸው፣ የዕለቱ ተሿሚዎች የመከላከያ ሠራዊት መተዳደሪያ ደንብ በሚፈቅደው መሰረት የመቆያ ጊዜያቸውን በመልካም ዲስፕሊን የሸፈኑና የማዕረግ መመልመያ መስፈርቱን ያሟሉ መስመራዊ መኮንኖችና ባለሌላ ማዕረግተኞች ሹመት የተፈቀደ መኾኑን መግለጻቸውን ከመከላከያ ሠራዊት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/