በኢጋድ አባል ሀገራት በቀውስ አያያዝና ግጭቶችን በማስቀረት ረገድ ለውጦች መታየታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶክተር) ገለጹ።

0
119

በኢጋድ አባል ሀገራት በቀውስ አያያዝና ግጭቶችን በማስቀረት ረገድ ለውጦች መታየታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶክተር) ገለጹ።

የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) አባል ሀገራት ርዕሳነ ብሔራት እና ርዕሳነ መንግሥታት 13ኛውን መደበኛ ስብሰባ አዲስ አበባ ላይ እያካሄዱ ነው።

በስብሰባው መክፈቻ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶክተር) እንደተናገሩት አባል ሀገራቱ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቀውስ አያያዝና ግጭቶችን በማስቀረት ረገድ ለውጦች መታዬታቸውን አመልክተዋል።

አባል ሀገራቱ በቀጣናው ሠላም እንዲሰፍንና ልማት እንዲጠናከር የሚያደርጉትን ጥረትም በስኬትነት ጠቅሰዋል።

አባል ሀገራት ኢትዮጵያ ተቋሙን ለበርካታ ዓመታት እንድትመራ አመኔታ ማሳደራቸውንም ዶክተር ዐብይ አድንቀዋል።

ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here