በኢትዮጵያ የተካሄደው 6ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሥርዓቱን በጠበቀ፣ በሰላምና ተዓማኒነት መጠናቀቁን የአፍሪካ ሕብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን ገለጸ።

150

በኢትዮጵያ የተካሄደው 6ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሥርዓቱን በጠበቀ፣ በሰላምና ተዓማኒነት መጠናቀቁን የአፍሪካ ሕብረት የምርጫ
ታዛቢ ቡድን ገለጸ።
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 16/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአፍሪካ ሕብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን በአዲስ አበባና በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች
ከቅድመ ምርጫ ዝግጅት ጀምሮ የምርጫውን የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱን ተዘዋውሮ መታዘቡን ገልጿል።
ምርጫው ሰላማዊና ቅደም ተከተላዊ ሥርዓቱን ተከትሎ መከናወኑን ነው የሕብረቱ የምርጫ የታዛቢ ቡድኑ ዛሬ በሰጠው
የመጀመሪያ መግለጫ ያሳወቀው።
የታዛቢ ቡድኑ መሪ የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴገን ኦባሳንጆ እንደገለጹት፤ ምርጫው ሥርዓቱን በጠበቀ፣ በሰላምና
ተዓማኒነት መጠናቀቁን ገልጸዋል።
ታዛቢ ቡድኑ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጠጣር በ2007 የሕብረቱ የዴሞክራሲ፣ ምርጫና አስተዳደር ቻርተር መሰረት ተከትሎ ነው
ምርጫውን የታዘበው።
ቡድኑ በአፍሪካ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ አስተዳደር በተመለከተ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጠጣር በ2002 ያወጣውን የመርህ
ድንጋጌም መሰረት አድርጓል ብሏል። ኢዜአ እንደዘገበው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m