ባሕር ዳር፡ ግንቦት 30/2012 ዓ.ም (አብመድ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ለ6 ሺህ 92 ሰዎች በተደረገ የላቦራቶሪ ምርመራ 86 የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋ፤ 63 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል፡፡ ሰባት ሰዎች ግን ሕይታቸው አልፏል
በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 20 ገብቷል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 1 ሺህ 647 በሕክምና ላይ ይገኛሉ፤ 27 ሕይወታቸው አልፏል፤ 344 ደግሞ አገግመዋል፡፡ 32 ሰዎች በጽኑ ሕክምና ክፍል ውስጥ እንደሚገኙም ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ዛሬ በአዲስ ቫይረሱ የተገኘባው 86 ሰዎች ዕድሜያቸው ከ7 እስከ 82 ዓመት የሆኑ 51 ወንዶችና 35 ሴቶች ናቸው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 66 ከአዲስ አበባ ሲሆኑ ሰባት ከኦሮሚያ ክልል፣ ሰባት ከትግራይ ክልል፣ አራት ከደቡብ ክልል፣ አንድ ከአማራ ክልል እና አንድ ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ናቸው፡፡
በኢትዮጵያ እስከዛሬ ለ142 ሺህ 960 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተደርጎላቸዋል፡፡
ባለፉት ሰባት ቀናት ብቻ 848 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ 16 ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸው አልፏል፡፡