በኢትዮጵያ ለሚኖሩ 1 ሚሊየን የውጭ ሃገራት ስደተኞች አስፈላጊው ጥበቃና እንክብካቤ እየተደረገ መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማጣሪያ ገለፀ፡፡

0
73

በኢትዮጵያ ለሚኖሩ 1 ሚሊየን የውጭ ሃገራት ስደተኞች አስፈላጊው ጥበቃና እንክብካቤ እየተደረገ መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማጣሪያ ገለፀ፡፡

ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 02/2013 ዓ.ም (አብመድ) ኢትዮጵያ ስደተኞችን ተቀብላ በማስተናገድ የቆየ ልምድ አላት፤ በአሁኑ ወቅት ከደቡብ ሱዳን፣ ከሶማሊያ፣ ከኤርትራ እና ከሱዳን መጥተው በ26 የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ለሚኖሩ ስደተኞች አስፈላጊው ጥበቃና እንክብካቤ እየተደረገላቸው መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማጣሪያ አመላክቷል።
ምግብ ነክ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ግብዓቶች እንደ መጠለያ፣ሕክምና፣ውኃ፣ የንጽሕና መጠበቂያ፣ትምህርት እና ሌሎች አገልግሎቶችን ጨምሮ ስደተኞቹ በአግባቡ እያገኙ መሆኑንም አስታውቋል።
ኢትዮጵያ በምትከተለው ፖሊሲ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ከጋራ መጠለያ ወጥተው በፈቀዱት ቦታ እንዲኖሩ እያደረገች መሆኑንም ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማጣሪያ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ