በአፍሪካና በቻይና መካከል ያለውን ትብብር ማሳደግ የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ።

0
45

ባሕርዳር: ጥር 03/2015 ዓ.ም  (አሚኮ)በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግ ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃመት ጋር ተወያዩ።

ሁለቱ ወገኖች በአፍሪካና ቻይና መካከል ያለውን ትብብር ማሳደግ የሚያስችል ስምምነትም ተፈራርመዋል።

አፍሪካና ቻይና በንግድ፣ በመሰረተ ልማትና በሌሎች ጉዳዮች ላይ በጋራ ከመስራታቸውም ባለፈ ጠንካራ የዲፕሎማሲ ግንኙነት መስርተዋል።

በዚህም ባለፉት ዓመታት የነበሩ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አፍሪካን በየዓመቱ የጎበኙ ሲሆን፤ የአዲሱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጉብኝት ለ33ኛ ጊዜ የተካሄደ ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግ ኢትዮጵያን ጨምሮ 5 ሀገራትን የሚጎበኙ ሲሆን፤ በዛሬው እለትም ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃመት ጋር ተወያይተዋል።

በቀጣይም በ4 የአፍሪካ ሀገራት ከሚያደርጉት ጉብኝት በተጨማሪ ከሌላኛው ቀጠናዊ ድርጅት ከአረብ ሊግ የሥራ ኀላፊዎች ጋር እንደሚወያዩ ኢቢሲ ዘግቧል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!