በአዲስ የኢትዮጵያ ትምሕርት ቤቶች ግንባታ አካል በሰሜን ወሎ ዞን መርሳ ከተማ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።

0
53

ወልድያ: ነሐሤ 05/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የትምሕርት ሚኒስትሩ ኘሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ የትምሕርት ጥራትን ለማሻሻልና የትምሕርት ተቋማትን ደረጃ የማሳደግ ሥራ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በትኩረት እየሠራ ነው ብለዋል።

ለዚህም በጦርነቱ ለተጎዱ አካባቢዎች ቅድሚያ በመስጠት በዛሬው ዕለት በሰሜን ወሎ ዞን መርሳ ከተማ መልካጨፌ ትምሕርት ቤት ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል።

አዲሱ የኢትዮጵያ ትምሕርት ቤቶች ግንባታ የስፖርት ማዘውተሪያ፣ የእርሻ ቦታ፣ የእደ ጥበብ ማልሚያና ሌሎችንም ያቀናጀ ነው ብለዋል ሚኒስትሩ።

ከትምሕርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ግንባታውን የሚያከናውነው ሰዎች ለሰዎች ግብረ ሰናይ ድርጅት መኾኑ ተገልጿል። የድርጅቱ የሕዝብ ግንኙነት አቶ ሙሉነህ ቶሎሳ የትምሕርት ቤቱ ግንባታ ወረዳው ወሰን አስከብሮ ካስረከባቸው የግንባታ ስፍራውን ካዘጋጀው በኋላ በአጭር ጊዜ እንደሚጠናቀቅ ገልጸው የመጀመሪያ ዙር 16 ሚሊየን ብር በጀት እንደተያዘለት ተናግረዋል።

ከግንባታም ባሻገር የመማሪያ ክፍሉና የአስተዳደር ቢሮው ሙሉ ቁሳቁስ አሟልቶ ለኅብረተሰቡ እንደሚያስረክብ አቶ ሙሉነህ ገልጸዋል።

የአካባቢው ሽማግሌ አቶ በላይ ሞላ ትምሕርት ቤቱ በጦርነት የተጎዳ እንደነበር ገልጸው አሁን ሊገነባ በታሰበው ግንባታ ደስተኛ ነን ብለዋል። የአካባቢው ማኅበረሰብም የራሱን ተሳትፎ እንደሚያደርግ ነው የተናገሩት።

ዘጋቢ:-ካሳሁን ኃይለሚካኤል

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/