በአዲስ አበባ ከተማ የአማራ ወጣቶች ማኅበር በአጣዬ እና አካባቢው ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ፡፡

0
114

በአዲስ አበባ ከተማ የአማራ ወጣቶች ማኅበር በአጣዬ እና አካባቢው ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 27/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአዲስ አበባ የአማራ ወጣቶች ማኅበር በአጣዬ እና አካባቢው በደረሰው የጸጥታ
ችግር ለተፈናቀሉ ወገኖች ሦስት ሚሊየን ብር የሚገመት የምግብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡
የማኅበሩ ፕሬዝዳንት ወጣት ዘነበ በለጠ የደረሰውን ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት አውግዟል፡፡ ለወገን ደራሽ ወገን መሆኑን ለማሳየት ድጋፍ
አድርገናል ነው ያለው፡፡
ድጋፉም በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ ለጋሽ የማኅበረሰብ ክፍሎች የተሰበሰበ መሆኑን ገልጿል፡፡ ድጋፉ ቀጣይነት እንዳለውም
ወጣት ዘነበ ተናግሯል፡፡
የኤፍራታና ግድም ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ጌታሰው አበበ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ ክረምት
ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ በመጠለያ ጣቢያ የሚኖሩ ወገኖች ችግር ላይ እንዳሉ ጠቁመዋል፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ድጋፍ በማድረግ
የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በአዲስ አበባ የአማራ ወጣቶች ማኅበር በአጣዬ እና አካባቢው ለተጎዱ ወገኖች ለአራተኛ ጊዜ ነው ድጋፍ ያደረገው፡፡
ማኅበሩ ከተመሰረተ ጀምሮ ችግር ውስጥ ላሉ የአማራ ክልል ነዋሪዎች ከ80 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል፡፡
ዘጋቢ፡- ገንዘብ ታደሰ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here