በአውስትራሊያ ሜልቦርን የሚኖሩ የደሴ ከተማ እና አካባቢው ተወላጆች ለተፈናቃይ ወገኖች ከ330 ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ ድጋፍ አደረጉ፡፡

0
79

ባሕር ዳር: ነሐሴ 23/2013 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትህነግ ቡድን ወረራ በፈጸመባቸው አካባቢዎች በርካቶችን ገድሏል፣ ሕጻናትንና ሴቶችን ደፍሯል፣ አፈናቅሏል፣ የግልና መንግሥት ንብረቶችን ዘርፏል፣ አውድሟል።

አሸባሪው ቡድን ከቤት ንብረታቸው ያፈናቀላቸውን ወገኖች የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ እንዲያገኙ ለማድረግ እየተሠራ ይገኛል።

በአውስትራሊያ ሜልቦርን የሚኖሩ የደሴ እና አካባቢው ተወላጆች በአሸባሪው የትህነግ ቡድን ወረራ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ330 ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ የቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል።

የአልባሳት፣ የምግብ ማብሰያና ሌሎች ቁሳቁስ ለተፈናቃይ ወገኖች ድጋፍ መደረጉን የድጋፉ አስተባባሪ አቶ አድማሱ አቢ ገልጸዋል።

ሌሎች በውጭ ሀገራት የሚኖሩ የደሴ እና አካባቢዋ ነዋሪዎችን በማስተባበር ችግር እየደረሰባቸው ለሚገኙ ወገኖች አስቸኳይ ድጋፍ እንዲያደርጉ እየሠሩ መሆናቸውንም አቶ አድማሱ አስታውቀዋል፡፡

ድጋፉን የተረከቡት ተፈናቃይ ወገኖች ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

ወራሪውና አሸባሪው የትህነግ ቡድን ከቀያቸው ቢያፈናቅላቸውም የደሴ ሕዝብ ያለውን እያካፈላቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ሳልሐዲን ሰይድ-ከደሴ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m