በአውሮፓ የተለያዩ ሀገራት የሚኖሩ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ተወላጆች በዲማ ግንባር ለሚገኙ የጸጥታ ኀይሎች ድጋፍ አደረጉ።

0
127

ባሕር ዳር: ነሐሴ14/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአውሮፓ የተለያዩ ሀገራት የሚኖሩ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ተወላጆች በዲማ ግንባር ለሚገኘው መከላከያ ሠራዊት ፣ለአማራ ልዩ ኀይል፣ ለሚሊሻና ፍኖ ድጋፍ አድርገዋል።

በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በዲማ ግንባር የሚገኘው የፋኖ አባል ታጋይ ታዴ ነጋሽ “ቀን ከሌሊት ፀሐይና ዝናብ ሳንል የሚመጣውን የሽብር ቡድን እየደመሰስን እንገኛለን ” ብለዋል።
ታጋይ ታዴ አሸባሪውን ቡድን እስከ መጨረሻው ሳንደመስስ እንቅልፍ አይኖረንም ነው ያሉት።

የጋንታ መሪ የሆኑት አማኑኤል ደነቀው በበኩላቸው “ጠላትን መቅበር ታሪካችን ነው” ብለዋል።

“ወንድሞቻችን ለኛ የሚያደርጉት ድጋፍ ይበልጥ ለድል እንድንተጋ አድርጎናል” ያለን ደግሞ ታጋይ ነጋሽ መዓዛ ነው። የድጋፉ ዋና አስተባባሪ አቶ ወንድም ገብረ መድህን በአውሮፓ የተለያዩ ሀገራት የሚኖሩ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ተወላጆች በግንባር ለሚገኙ የጸጥታ ኀይሎች 232 ሽህ ብር ወጭ በማድረግ የሬሽን እና ልዩ ልዩ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸውን ነው የገለጹት።

አቶ ወንድም ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል፡፡

በግንባር የሚገኙ የጸጥታ ኀይሎች እየተደረገላቸው ላለው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ያየህ ፈንቴ-ከዲማ ግንባር

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here