በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች እና በኅልዉና ዘመቻው የተሳተፉ አካላትን መደገፍ የሚያስችል የንግድ እና ባዛር በጎንደር ከተማ ተጀምሯል።

0
36

ጎንደር፡ ጥር 07/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ከንግድ እና ባዛሩ ከሚገኘው ገቢ 25 በመቶ የሚሆነው በኅልዉና ዘመቻው ለተሳተፉ ድጋፍ ይውላል ተብሏል። ከ70 በላይ የዉጭ ሀገራት እና ከ200 በላይ የሀገር ዉስጥ ነጋዴዎች በንግድ እና ባዛሩ እንደሚሳተፉም ታውቋል።

ንግድ እና ባዛሩን የከፈቱት የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዘውዱ ማለደ በንግድ እና ባዛሩ የሚሳተፉ ዜጎች በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የተጎዱ ወገናቸውን እና በኅልዉና ዘመቻው የተሳተፉ ጀግኖችን እየደገፉ እንደሆነ መረዳት አለባቸው ብለዋል፡፡

ንግድ እና ባዛሩ መዘጋጀቱ የከተማው ነዋሪ ወገኑን እየደገፈ በተመጣጣኝ ዋጋ መገበያየት የሚያስችለው መሆኑንም ገልጸዋል።

ወደ ከተማው የሚገቡ የዳያስፖራ አባላትም በዓሉን በጥሩ ሁኔታ እንዲያሳልፉ ከተማ አስተዳደሩ ዝግጅት ማድረጉን ነው የተናገሩት። ሆቴሎችም እንግዶቻቸውን ለመቀበል እስከ 30 በመቶ ቅናሽ አድርገው እየተቀበሉ እንደሆነም ነው የነገሩን።

የቱሪዝሙ እንቅስቃሴ በኮሮና ቫይረስ መከሰት እና በአሸባሪው ቡድን ምክንያት ተዳክሞ የነበረ ቢሆንም በቀጣይ የተሻለ እንቅስቃሴ እንዲኖር ትልቅ መነቃቃት መፍጠሩን አስረድተዋል።

ንግድ እና ባዛሩ ለአሥር ቀናት እንደሚቆይም ታውቋል፡፡

ዘጋቢ፡- ዳንኤል ወርቄ-ከጎንደር

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq በዌብሳይት amharaweb.com በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
://ameco.bankofabyssinia.com/