በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ሃይንከን ቢራ አክሲዎን ማኅበር ድጋፍ አደረገ፡፡

0
87

ወልድያ፡ ጥር 05/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ሃይንከን ቢራ አክሲዎን ማኅበር 5 ነጥብ 7 ሚሊዬን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡

ሃይንከን ቢራ አክሲዎን ማህበር አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጉዳት ላደረሰባቸው በሸዋሮቢት፣ በኮምቦልቻ፣ በደሴ፣ በሰቆጣ እና በወልድያ ከተሞች ለሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች 5 ነጥብ 7 ሚሊዬን ብር ግምት ያላቸው የምግብ እና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ ሰጥቷል፡፡ 1ሺህ 500 የኅብረተሰብ ክፍሎችን ተደራሽ ማድረጉም ተገልጿል፡፡

በወልድያ ከተማ በተደረገው ድጋፍ ላይ የተገኙት የሃይንከን ቢራ አክሲዎን ማኅበር የምስራቅ አማራ አካባቢ ሽያጭ ኀላፊ አቶ ይመር ሽፈራው አክሲዎን ማኅበሩ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ቢሆንም ከአክሲዎን ማኅበሩ ጉዳት በላይ በአካባቢው ማኅበረሰብ የተከሰተው ጉዳት አሳሳቢ በመሆኑ የእለት ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል ፡፡

ከእለት ድጋፍ ባለፈም መልሶ በመገንባትና በማቋቋም ሂደት አክሲዎን ማኅበሩ የድርሻውን እንደሚወጣ ነው ኀላፊው የተናገሩት፡፡

ድጋፍ የተደረገላቸው የኅበረተሰብ ክፍሎችም ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ባለ ዓለምየ-ከወልድያ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/