በአሜሪካ የሚኖሩ “በቃን” የአማራ የአደጋ ጊዜ ገንዘብ ማሰባሰቢያ ለተፈናቀሉ ወገኖች የ10 ሚሊየን ብር የምግብና አልባሳት ድጋፍ አደረገ።

0
69
.ም (አሚኮ) ሽብርተኛው ትህነግ በፈጸመው ወረራ ዜጎች ሕይወታቸውን እና ንብረታቸውን አጥተዋል፡፡ በርካቶች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ለችግር ተዳርገዋል።
የአማራ መፈናቀልና ሞት ያንገበገባቸው በአሜሪካ የሚኖሩ እና የተለያዩ የአማራ ተወላጆች ማኅበራት “በቃን!” የአማራ የአደጋ ጊዜ ገንዘብ ማሰባሰቢያን በማቋቋም ተፈናቃይ ወገኖችን እየደገፉ ይገኛሉ።
ከተለያየ አካባቢ ተፈናቅለው ለሚገኙ ወገኖች የ10 ሚሊየን ብር የምግብና አልባሳት ድጋፍም ተደርጓል። ድጋፉ በተለየ መልኩ ለሕጻናት፣ ለአረጋውያን፣ ለእናቶችና ለአካል ጉዳተኞች የተደረገ ነው ተብሏል።
በአሜሪካ በሚገኘው “በቃን!” የአማራ የአደጋ ጊዜ ገንዘብ ማሰባሰቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት ጌታቸው በየነ በአሜሪካ የአማራ ማኅበራት በአማራው ላይ የሚደርሰው ሞትና መፈናቀል “በቃን!” ብለው ተነስተዋል ነው ያሉት።
ፕሬዚዳንቱ በቀጣይም የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ለማድረግ እንደሚሠሩ እና ከዚህ በፊትም በተለያዩ አካባቢዎች ድጋፍ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡
አቶ ጌታቸው እንደገለጹት መንግሥት አሁንም ሽብርተኛው ትህነግ የወረራቸው አካባቢዎች ነጻ ሊያወጣ ይገባል፤ ችግሩን ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ማሳወቅ ላይ ሊሠራ ይገባል፤ በችግር ላይ ላለው ሕዝብ ሁሉም መጮኽ አለበት፤ የማኅበረሰብ አንቂዎችም ትክክለኛውን ችግር ሊያሳውቁ ይገባል ነው ያሉት።
ሌላው የማኅበሩ አባል ሰጥአርጌ አስማረ እንደነገሩን ማኅበሩ እስከ አሁን ከ1 ነጥብ 1 ሚሊዮን ዶላር በላይ ድጋፍ ሰብስቧል፤ ከዚህ ተቀንሶ ደግሞ 600 ሺህ ዶላር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ በተለያዩ አካባቢዎች ለተጠለሉ ተፈናቃዮች የምግብና የአልባሳት ድጋፍ እየተደረገ ነው ብለዋል።
ዘጋቢ፦ አዳሙ ሽባባው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ