በአማራ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ተቋቋመ።

0
485

በአማራ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ተቋቋመ።
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 17/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በ6ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በአማራ ክልል የሚወዳደሩ ዘጠኝ ተፎካካሪ
የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አቋቋሙ።
በምርጫው ሂደት ፓርቲዎች የሚያጋጥሙ ችግሮችን በጋራ በመፍታት ምርጫው ሰላማዊና በመተማመን ላይ የተመሰረተ ሆኖ
እንዲጠናቀቅ ለማስቻል ምክር ቤቱ መቋቋሙ ተመልክቷል።
የጋራ ምክር ቤቱን ትናንት የመሰረቱት የኢትዮጵያ ነፃነት ፓርቲ፣ የኢትዮጵያ ዲሞክራት ህብረት፣ ኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ
ፓርቲ፣ ብልፅጽግና ፓርቲ፣ ህብር ኢትዮጵያ፣ መላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ፣ የኢትዮጵያ
ዲሞክራሲ ሃይሎች ንቅናቄና እናት ፓርቲ ናቸው።
የእናት ፓርቲ የሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ አስተባባሪ አቶ ጀምበሩ አለማየሁ ለኢዜአ እንደገለፁት የዘንድሮው ምርጫ ከዚህ በፊት
ከነበሩት የምርጫ ሂደቶች የተሻለ ሁኔታ ይስተዋልበታል።
በሃገሪቱ አዲስ የፖለቲካ ምህዳር እንዲሰፋ የፖለቲካ ፓርቲዎች እርስ በእርስ መቃወም ላይ መሰረት ካደረገ እንቅስቃሴ
በመላቀቅ ተፎካካሪ ሆኖ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
የምክር ቤቱ መቋቋም እርስ በእርስ ተቀራርቦ በመስራት በእንቅስቃሴ ሂደት ችግር እንዳይፈጠር ቢፈጠርም በሰከነ አግባብ
በመወያየት ለመፍታት ትልቅ ሚና እንዳለው አመልክተዋል።
“እንዲሁም እርስ በእርስ ከመጠራጠር፣ ከመጠላለፍና ጥል ከመፍጠር በመላቀቅ የሰለጠነ የፖለቲካ እንቅስቃሴ እንዲፈጠርም
ያግዛል” ብለዋል።
ከሁሉም በላይ በዚህ ምርጫ አሸናፊው ህዝብ እንዲሆን እንዲሁም ምርጫው ዴሞክራሲያዊ፣ ነፃና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ
እየተደረገ ያለውን ጥረት በማጎልበት ምክር ቤቱ የጎላ ድርሻ እንዳለው አብራርተዋል።
የአማራ ዴሞክራሲ ንቅናቄ (አዴሃን) ሊቀመንበርና የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ ሆነው የተመረጡት አቶ ተስፋሁን አለምነህ
በበኩላቸው አሁን ያለው የፖለቲካ ድባብ ምርጫው የተሻለ ተስፋ እንዲጣልበት ያደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ዘገባው የኢዜአ
ነው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here