ባሕር ዳር: የካቲት 30/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል በ2015 በጀት ዓመት 166 አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት ታቅዶ እየተሠራ መኾኑን ርእሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) በምክር ቤቱ ጉባዔ ላይ ገልጸዋል።
አጠቃላይ በዓመቱ ለመገንባት ከታቀዱት 166 ትምህርት ቤቶች ውስጥ 84 የሚኾኑት በግማሽ ዓመቱ የሚጠናቀቁ ናቸው ብለዋል። ከ84ቱ ውስጥ 45 የሚኾኑት እስከ ሩብ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ መጠናቀቃቸውን ገልጸዋል።

ርእሰ መስተዳድሩ እነዚህ ትምህርት ቤቶች የሚገነቡት በመንግሥት እንዲሁም በኅብረተሰቡ እና በአጋር አካላት ትብብር እንደኾነም አስረድተዋል።
ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!