በአማራ ክልል ከ11 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ወገኖች የዕለት ምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው የክልሉ አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

0
153

ባሕር ዳር: የካቲት 28/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በሽብርተኛው የትግራይ ቡድን ወረራ የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ ቀያቸው የመመለሱ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉን የአማራ ክልል አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር እያሱ መስፍን ገልጸዋል፡፡
በማንነታቸው ምክንያት ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ ወገኖችም በአብዛኛው በመጠለያ ጣቢያ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡
በአሸባሪው ቡድን ወረራና ከተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ በክልሉ ከ11 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ ወገኖች የዕለት ምግብ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ብለዋል፡፡
ለእነዚህ ወገኖች በአንድ ወር ብቻ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ኩንታል በላይ እህል ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡
እስካሁን በማኅበረሰቡ፣ በግል ድርጅቶች እና ረጅ ድርጅቶች ይቀርብ የነበረው የምግብ ድጋፍ ወደ አንድ ቋት በማስገባት እየቀረበ መኾኑንም ተናግረዋል፡፡ ከዚህ ውስጥ 70 በመቶውን የፌዴራሉ መንግሥት እያቀረበ ሲኾን
30 በመቶው በክልሉ መንግሥት እየሸፈነ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡
በአሁኑ ወቅትም ማኅበረሰቡ በመጠለያ ጣቢያዎች ለተጠለሉ ተፈናቃዮች ምግብ እና ምግብ ነክ ቁሳቁስ እያቀረበ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ ይኽንንም አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ትርንጎ ይፍሩ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/