በአማራ ክልል ከአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ነጻ በወጡ አካባቢዎች የፖለቲካ፣ የአስተዳደርና የጸጥታ መዋቅር በመዘርጋት ሕዝባዊ አገልግሎት መሰጠት መጀመሩን በብልጽግና ፓርቲ የክልሉ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

0
104

ታኅሣሥ 15/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሞላ መልካሙ እንደተናገሩት፤ የወገን ጦር በወሰደው እርምጃ በሽብር ቡድኑ የተወረሩ የክልሉ አካባቢዎች ከአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ነጻ ወጥተዋል።
በየደረጃው ያሉ የክልሉ አመራሮችም ለመከላከያ፣ ለልዩ ኃይል፣ ለሚሊሻ፣ ለፋኖና ሌሎች የጸጥታ ኃይሎች ድጋፍ በማድረግ ለተገኘው ድል አጋዥ ሚና መጫወታቸውንም አውስተዋል።
ከአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ነጻ በወጡ 98 በመቶ አካባቢዎች የፖለቲካ፣ አስተዳደርና ጸጥታ መዋቅር በመዘርጋት የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ ምቹ ሁኔታ እንደተፈጠረ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
በሰሜን ሸዋና ደቡብ ወሎ ዞኖች ውስጥ ያሉ ወረዳዎች፣ በኮምበልቻና ደሴ ከተሞች፣ በሰሜን ወሎ ዞን፣ በኦሮሞ ብሔረሰብና ዋግ ብሔረሰብ አስተዳደሮች የፖለቲካ፣ የአስተዳደርና የጸጥታ መዋቅሩን ወደ ሥራ ማስገባት መቻሉንም ነው የተናገሩት።
በጠቅላይ ሚኒስትሩ የዘመቻ መሪነት ጠላት ከክልሉ ተጠራርጎ መውጣቱን ተከትሎ የክልሉ መንግሥትና መሪ ድርጅት በስድስት ጉዳዮች ላይ በማተኮር ሥራዎች መከናወናቸውን አስገንዝበዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation