በአማራ ክልል ባለፉት ወራት ወደ ውጭ ሀገራት ከተላኩት ምርቶች 92 ነጥብ 9 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ገለጸ።

0
52

ደሴ: ግንቦት 15/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኮምቦልቻ ከተማን የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለባለ ሃብቶች በማስተዋወቅ የከተማዋን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ለማሳደግ ያለመ የንቅናቄ ፎረም ከባለድርሻ አካላት ጋር በኮምቦልቻ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው።

የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ሙሐመድ አሚን የከተማውን ኢንቨስትመንት የማነቃቃት ሥራዎች እየተከናወኑ መኾኑን ገልጸዋል። እስካሁን ከ865 ሄክታር በላይ መሬት ለባለሃብቶች ተሰጥቷል ብለዋል። ባለ ሃብቶቹ ከ50 ቢሊየን ብር በላይ ኢንቨስት ማድረጋቸውንም ገልጸዋል።

ይህ ፎረም ባለ ሃብቶች ያሉባቸውን ችግሮች ለመለየትና በከተማ አሥተዳደሩ በኩል ያሉ ውስንነቶችን በመለየት ለኮምቦልቻ ከተማ ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴው ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ያግዛልም ነው ያሉት።

የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኀላፊ አቶ እንድሪስ አብዱ የኢንቨስትመንት ፎረሙ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ምክንያት የተቀዛቀዘውን የአካባቢውን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ከማነቃቃት ባሻገር በዘርፉ የሚታዩ ፈታኝ ሁኔታዎችን በመለየትና መፍትሔ በማመላከት የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ወደ ሙሉ ትግበራ እንዲገቡ ለማስቻል ያለመ መኾኑን ገልጸዋል።

በአማራ ክልል ከ75 ሺህ በላይ ለሚኾኑ ዜጎች ቋሚ የሥራ እድል የፈጠሩ በአነስተኛ፣ በመካከለኛና በከፍተኛ ደረጃ የሚንቀሳቀሱ 3 ሺህ 600 አምራች ኢንዱስትሪዎች መኖራቸውን ያነሱት ቢሮ ኀላፊው እነዚህ አምራች ኢንዱስትሪዎች ባለፉት ወራት ወደ ውጭ ከላኩት ምርት 92 ነጥብ 9 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል።

በውይይቱ የኀይልና ብድር አቅርቦት ችግር፣ የግብዓት እጥረት፣ የአገልግሎት አሰጣጡ የተቀላጠፈ አለመኾን በባለሃብቶች ተነስተዋል።

ችግሮቹን በዘላቂነት ለመፍታት የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደርና የክልሉ መንግሥት በቅንጅት እየተሠራ መኾኑ ተገልጿል።

በፌዴራል መንግሥት በኩል መመለስ የሚገባቸው ችግሮች መፍትሔ እንዲያገኙ ለማስቻል ጥረት እየተደረገ መኾኑም ተነግሯል።

ዘጋቢ:- አሊ ይመር – ከኮምቦልቻ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/