በአማራ ክልል በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የደረሱ ጉዳቶችን እና በክልሉ ሊለሙ የሚችሉ ፀጋዎችን የሚያሳይ አውደ ርዕይ በባሕር ዳር እየተካሄደ ይገኛል።

0
139

ባሕር ዳር፡ ጥር 01/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አውደ ርዕዩ እየተጎበኘ የሚገኘው በክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፣ በነዋሪዎችና በዳያስፖራው ነው። አውደ ርዕዩ እየተካሄደ የሚገኘው በባሕር ዳር ከተማ ነው። በክልሉ መንግሥት የተዘጋጀው አውደ ርዕይ ላይ በአማራ ክልል በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የደረሰው ጉዳት፣ የመሰረተ ልማት ውድመት፣ በክልሉ ሊለሙ የሚችሉ ፀጋዎችና ሌሎችንም ያካተተ ነው፡፡

የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ጌታቸው ጀምበር (ዶ.ር) አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት አድርሷል ብለዋል፡፡ በአማራ ሕዝብ ላይ መሰል ጉዳቶች እንዳይፈጸሙ የአማራ ሕዝብ ውስጣዊ አንድነቱን መጠበቅ እንዳለበት ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ አሳስበዋል። “የተለያዩ አጀንዳ እየሰጡ ሊከፋፍሉን የሚፈልጉ አካላትን ቦታ ልናሳጣቸው ይገባል” ነው ያሉት።

“የሌላውን አጀንዳ ከተቀበልን፣ ውስጣችን ከተከፋፈለ ማሸነፍ አንችልም። ኅልውናችንን ለማስቀጠል፣ ኢትዮጵያን እንደ ሀገር ለማስቀጠል መደማመጥ ይጠበቅብናል” ብለዋል።

ሕዝቡ ከጥር 1 እስከ ጥር 5/2014 ዓ.ም ድረስ የሚቆየውን አውደ ርዕይ እንዲጎበኝ ዶክተር ጌታቸው ጥሪ አቅርበዋል።

አቶ ሐብታሙ አመራ ሀገራዊ ጥሪውን ተቀብለው ነው ከአሜሪካ የመጡት። ለወገን ጦር 500 ሺህ የሚገመት የሕክምና ቁሳቁስና አልባሳት ድጋፍ አድርገናል ብለዋል።

ወደ ሀገር የገባው ዳያስፖራ የተጎዱ ዜጎችን ለመደገፍ፣ የወደሙትን ንብረቶች ለመተካት እየሠራን ነው ሲሉም ተናግረዋል። ከመጡበት ሀገር ሲመለሱ የተመለከቱትን ኹሉ ለዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ እንደሚያስረዱም አቶ ሐብታሙ ገልጸዋል።

ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/