በአማራ ክልል በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ በማቋቋሙ ተግባር ላይ ሁሉም የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ።

88

ባሕር ዳር: ግንቦት 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ባደረሰው ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት ላይ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ስዩም መኮንን መግለጫ እየሰጡ ነው፡፡

አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በአማራ ክልል በፈጸመው ወረራ በርካታ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመት ማድረሱን ዩኒቨርስቲዎች፣ የክልሉ መንግሥት እና የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ለአምስት ወራት በጥናት ማረጋገጡን
አቶ ስዩም መኮንን በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡ ጥናቱ ሳይንሳዊና ተአማኒነት ባለው መልኩ መከናወኑንም ጠቅሰዋል።

አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በወረራ በቆየባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ከ828 ሺህ በላይ በሚኾኑ ወገኖች ላይ ቀጥታ ጉዳት ማድረሱን በጉዳዩ ላይ የተካሄደው ጥናት አረጋግጧል።

ከ288 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ቁሳዊ ውድመት ማድረሱም በጥናቱ ይፋ ኾኗል።
ጥናቱ ጉዳቱን ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ማስገንዘብ፣ መልሶ የማቋቋም ሥራ በክልሉ አቅም ብቻ የሚቻል ባለመኾኑ የሁሉንም ርብርብ የሚጠይቅ መኾኑንም ያረጋግጣል ብለዋል አቶ ስዩም።

አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የአማራን ሕዝብ አንገት ለማስደፋት ያደረገው ጥረት አለመሳካቱንም ሕዝቡ በመልሶ ማቋቋሙ ሥራ እያረጋገጠ ነዉ ብለዋል። እየተካሄደ ባለው የመልሶ ማቋቋም ተግባር ላይም ሁሉም የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል።

ዘጋቢ:–የማነብርሃን ጌታቸው

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/