በአማራና አፋር ክልሎች የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮችና የኦፕቲካል ፋይበር የጥገና ሥራ ተጠናቀቀ፡፡

0
109

መጋቢት 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራና አፋር ክልሎች የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ለመጠገን ለመለዋወጫ አቅርቦት የወጣውን ወጪ ሳይጨምር ለሥራው ብቻ ከ6 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ መደረጉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኀይል አሰታወቀ።
በአሸባሪው ቡድን ከፍተኛ ውድመት አጋጥሞ የነበረውን የከፍተኛ ኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮችና የኦፕቲካል ፋይበር ገመዶች የመጠገን ሥራ ተጠናቅቋል፡፡
የኦፕቲካል ፋይበር መስመር ጥገናው በሳምንት አንድ ቀን ብቻ ለተወሰኑ ሰዓታት ኤሌክትሪክ በማቋረጥ ሲሠራ ቆይቶ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኀይል ገልጿል፡፡
ከደብረሲና – ሸዋሮቢት – ከሚሴ – ኮምቦልቻ – አቀስታ – ዓለም ከተማ ባለ132 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ፤ ከደብረብርሃን – ኮምቦልቻ – ሠመራ እና ከኮምቦልቻ – አላማጣ እስከ ቆቦ ድረስ ባለ 230 ኪሎ ቮልት መስመር እንዲሁም ከደብረታቦር እስከ ጋሸና ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር በሚያልፍበት አካባቢ የሚገኙ ከተሞችና መንደሮች ላይ ከኅዳር 24/2014 ዓ.ም. ጀምሮ በተደረገው ጥገና አካባቢዎቹ ኤሌክትሪክ መልሰው እንዲያገኙ መደረጉ ይታወሳል፡፡
ከደሴ – ወልዲያ የ ባለ 66 ኪሎ ቪልት መስመር ጥገና በማካሄድ የወልዲያና አካባቢው ኃይል እንዲያገኙ ተደርገዋል፡፡
የመልሶ ጥገና ሥራውን ከተቋሙ ስምንት ሪጅኖች የተውጣጣ የጥገና ቡድን በከፍተኛ ርብርብ ሲያከናውን ቆይቷል፡፡
በአማራና አፋር ክልል የደረሰውን የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ለመጠገን ለመለዋወጫ አቅርቦት የወጣውን ወጪ ሳይጨምር ለሥራው ብቻ ከ6 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ መደረጉን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኀይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/