በኅልውና ዘመቻው ለተሰው የጀግኖች ልጆች ማሳደጊያ የህፃናት መርጃ ማዕከል በጎንደር ሊገነባ ነው።

0
200

ባሕርዳር፡ ጥር 13/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በኅልውና ዘመቻው መስዋአትነት ከፍለው ለሀገር ውለታ ለከፈሉ ጀግኖች አርበኞች ልጆቻቸውን ለማሳደግ የሚውል የህፃናት መርጃ ማዕከል ሊገነባ ነው።

ነዋሪነታቸው በለንደን ሀገር የሆኑ ወ/ሮ ባንችአምላክ ይልማ ወላጆቻቸውን ለሀገር ማሰከበር ሲባል መስዋእትነት ለከፈሉ ጀግኖች አርበኛ ልጆች በጎንደር ከተማ የህፃናት መርጃ ማዕከል ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ዛሬ ተቀምጧል።

የመርጃ ማዕከሉ የመሰረት ድጋይ በጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ዘውዱ ማለደ የተቀመጠ ሲሆን ባንቺ የህፃናት መርጃ ማዕኩል የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል።

የህፃናት መርጃ ማዕከሉ በ1ሽ 500 ካሬ መሬት ላይ የሚያርፍ ነው። የከተማ አስተዳደሩ የመስሪያ ቦታውን ሰጥቷል።

በመርጃ ማዕከሉ ከ100 በላይ ለሚኾኑ ህፃናት አገልግሎት እንደሚሰጥ ተገልጿል። 22ቱ ህፃናት በጎንደር ከተማ ሌሎቹ በአካባቢው በሚገኙ ዞኖችና ወረዳዎች የሚገኙ ህፃናት መኾናቸው በመሰረት ድጋይ ማስቀመጥ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተመላክቷል። መረጃው የጎንደር ከተማ ኮሙኒኬሽን ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!