“በችግር ውስጥ ሆነን ያደረግነው ሰላማዊ ምርጫ ለሌሎች ሀገራት ምሳሌ የሚሆን ነው” የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር

0
32
“በችግር ውስጥ ሆነን ያደረግነው ሰላማዊ ምርጫ ለሌሎች ሀገራት ምሳሌ የሚሆን ነው” የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 16/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ምርጫው በሰላም በመጠናቀቁና ሕዝቡ ላደረገው አስተዋጽዖ ምስጋና አቅርቧል።
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ታደሰ ገብረፃድቅ ከአሚኮ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት እንደ ሀገር ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ሆነን እንደ ዞን ደግሞ የፀጥታ ስጋት ውስጥ ሆነን ያካሄድነው ምርጫ በሰላም መጠናቀቁ ለሌሎች ሀገራትም ምሳሌ የሚሆን ነው ብለዋል።
በምርጫው ሂደት ላይ የሕዝቡ ተሳትፎ ወሳኝ ነበር ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ለዚህ ተግባር አስተዋጽዖ ለነበራቸው ምስጋና አቅርበዋል።
በሰሜን ሸዋ ዞን ደረጃ የጎላ ችግር አለማጋጠሙን ያወሱት አቶ ታደሰ በምርጫ ወቅት ቅስቀሳ ለማድረግ የሞከሩ አካላት በሕግ እንዲጠየቁ ተደርጓል ብለዋል።
በመርሃ ቤቴ መንዝ ቀያና ምንጃር ሸንኮራ ወረዳዎች መሰል ችግሮች አጋጥመው እንደነበር ተናግረዋል።
ከምርጫ ማግስት ሕዝቡ የትላንት ሰላም ወዳድነቱን እንዲያስቀጥል ጠይቀዋል።
በዞኑ 8 የፖለቲካ ፓርቲዎች የተወዳደሩ ሲሆን የብሄራዊ ምርጫ ቦርድን ውጤት መጠበቅ እንደሚገባ ተናግረዋል።
ማሕበረሰቡ ወደተለመደ ስራው ተመልሶ የልማት ተግባራትን ማከናወን እንዳለበትም አሳስበዋል።
በዞኑ በሁሉም ምርጫ በተካሄደባቸው አካባቢዎች ሌትና ቀን ሲሰሩ ለነበሩ የምርጫ አስፈፃሚዎች ታዛቢዎችና የፖለቲካ ፓርቲዎች ምስጋናም አቅርበዋል።
ዘጋቢ:– ኤሊያስ ፈጠነ–ከደብረ ብርሃን
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here