በቶክዮ ኦሎምፒክ ሀገሪቱ የለመደችውን ድል ለማስመዝገብ በርትቶ መሥራት እንደሚገባ ፕሬዝዳንቷ መልዕክት አስተላለፉ፡፡

0
56

ባሕር ዳር: የካቲት 08/2012 ዓ.ም (አብመድ) ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን የመጀመሪያው ችቦ ዛሬ ለኩሰዋል፡፡

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የኦሎምፒክ ቡድኑን የቶክዮ 2020 የመጀመሪያውን ችቦ ነው ዛሬ ጠዋት መስቀል አደባባይ ላይ የለኮሱት፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ለኦሎምፒክ ቡድኑ ድጋፉን በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶክተር) በኩል ማሳየቱን ያስታወሱት ፕሬዝዳንቷ እርሳቸውም በቻሉት ሁሉ እንደሚደግፉ ተናግረዋል፡፡

“በዓለም መድረክ ላይ ሰንደቅ ዓላማችንን ከማውለብለብ ባሻገር ያስለመዳችሁንን ድል እንድታጎናፅፉን እንፈልጋለን፤ ከዛሬዋ ቀን ጀምሮ በርትታችሁ ሥሩ” በማለትም አበረታትተዋቸዋል፡፡

የኦሎምፒክ ችቦውን በቀጣይ የሚለኩሰው የድሬዳዋ ከተማ አስተዳድር ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር መረከቡን ከአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here