‹‹በሳዑዲ አረቢያ በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎችን በአጭር ጊዜ ለመመለስ እየተሠራ ነው›› አምባሳደር ሌንጮ ባቲ

0
73

የካቲት 18/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በሳዑዲ አረቢያ በእስር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዜጎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ከሀገሪቱ መንግሥት ጋር በቅርበት እየተሠራ መኾኑን በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ።

በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሌንጮ ባቲ ለኢፕድ በሰጡት አስተያየት፤ በተለያየ ምክንያት በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ገብተው ለእስርና ለእንግልት የተዳረጉ ኢትዮጵያውያንን በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ የኢትዮጵያ መንግሥት ከሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ጋር በቅርበት እየሠራ ነው።

ከሳዑዲ የሚመለሱ ዜጎችን በተመለከተ ከተመለሱ በኋላ ችግር ላይ እንዳይወድቁ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የሚመራ ኮሚቴ ተቋቁሞ ከክልሎች ጋር ወደ ሥራ ተገብቷል ብለዋል።

በእሳቸው የሚመራው በሳዑዲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሠራተኞችን ያካተተው ኮሚቴም በጉዳዩ ዙሪያ ከሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ጋር በቅርበት እየሠራ መኾኑን ገልጸዋል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/