በሲዳማ ክልል የድምጽ አሰጣጥ ሂደት ተጠናቀቀ።

0
30

በሲዳማ ክልል የድምጽ አሰጣጥ ሂደት ተጠናቀቀ።

ባሕር ዳር: ሰኔ 15/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በሲዳማ ክልል በድምጽ መስጫ ወረቀት እጥረት ምክንያት ምርጫው በተቋረጠባቸው ጣቢያዎች ምርጫው ዛሬም ቀጥሎ በማካሄድ ማጠናቀቅ መቻሉን በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማና ደቡብ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ትናንት በሲዳማ ክልል በቁሳቁስ እጥረት ምክንያት የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱን ለዛሬ ያስተላለፈው በክልሉ 19 የምርጫ ክልሎች ስር በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ነው።

በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማና ደቡብ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍሬው በቀለ እንደተናገሩት ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ በ19ኙ የምርጫ ክልሎች ሥር በሚገኙ 1 ሺህ 998 ጣቢያዎች የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ሲካሄድ ቆይቶ ማጠናቀቅ ተችሏል።

ትናንት ያልመረጡ ነዋሪዎች ቦርዱ በላከው የድምጽ መስጫ ወረቀት ዛሬ ድምጽ መስጠታቸውን አስታውቀዋል።

በአሁኑ ሰዓት በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ምርጫ ታዛቢዎች በተገኙበት ድምጽ የተሰጠባቸው ሳጥኖችን በማሸግ ለቆጠራ እየተዘጋጁ እንደሚገኙም ጠቁመዋል።

በጣቢያዎቹ ሌሊቱን ቆጠራውን በማከናወን ውጤቱን ነገ ጠዋት ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግም አቶ ፍሬው መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here