በሰሜን አሜሪካ የአማራ ማኅበር ለደባርቅ ሆስፒታል የምግብና የአልባሳት ድጋፍ አደረገ።

0
44

ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 14/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን አሜሪካ የአማራ ማኅበር የደባርቅ ሆስፒታል ለህልውና ዘመቻው እየሰጠ ያለውን አገልግሎት ለማገዝ 150 ሺህ ብር የሚገመት የምግብ እና የአልባሳት ድጋፍ አድርጓል። ድጋፉን ለሆስፒታሉ ያስረከቡት የማኅበሩ ተወካይ ስጦታው ገብሬ ናቸው፡፡ አሸባሪውን ትህነግ በግንባር እየተፋለሙ ላሉት የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና ፋኖ አጋርነቱን ለመግለጽ ማኅበሩ ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

ማኅበሩ በቅርበት በመሆን ለጸጥታ አካላት የሕክምና አገልግሎት ለሚሰጡት ጎንደር፣ ደብረ ታቦር እና ደሴ ሆስፒታሎች የ1 ሚሊዮን ብር የምግብና አልባሳት ድጋፍ እንደሚያደርግም ተወካዩ ገልጸዋል።

የደባርቅ ጠቅላላ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ መኩሪያ አማረ እንዳሉት በሰሜን አሜሪካ የአማራ ማኅበር አጋርነቱን አሳይቷል፤ ድጋፉም ሆስፒታሉ በህልውና ዘመቻው እየሰጠ ያለውን አገልግሎት እንደሚያጠናክረውም ገልጸዋል።

ዘጋቢ፦ አዳሙ ሽባባው-ከደባርቅ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m