በርንማውዝ አሸንፎ በደረጃ ሰንጠረዡ 3ኛ ላይ ተቀመጠ፤ ኤሲ ሚላን የፀረ ዘረኝት ግብረ ኃይል ለማቋቋም ወሰነ፡፡

163
ነጭመደበኛ
ነጭመደበኛ

ባሕር ዳር፡ መስከረም 10/2012 ዓ.ም (አብመድ) የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ 6ኛ ሳምንት አንድ ጨዋታ ትናንት ተካሂዷል፤ ከሜዳው ውጭ ሳውዛምፕተንን የገጠመው በርንማውዝ 3ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፎ በደረጃ ሰንጠረዡ 3ኛ ላይ ተቀምጧል፤ ውጤቱም በሳውዛምፕተን ላይ የተቀዳጀው የመጀመሪያ ድል ሆኖለታል፡፡

በፕሪሚዬር ሊጉ ዛሬ በርከት ያሉ የ6ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ፤ ሌሲስተር ሲቲ ከቶተንሀም ሆትስፐርስ፣ በርንሌይ ከኖርዊች ሲቲ፣ ኤቨርተን ከሼፍ ዩናይትድ፣ ማንቸስተር ሲቲ ከዋትፎርድና ኒውካስል ዩናይትድ ከብራይተን የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች የዛሬ መርሀ ግብሮች ናቸው፡፡

ፕሪሚዬር ሊጉን ሊቨርፑል በ15 ነጥብ ይመራል፤ ማንቸስተር ሲቲ በ10 ነጥብ ይከተላል፤ በርንማውዝ በእኩል 10 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጦ 3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ ቶተንሀም ሆትስፐርስ፣ ማንቸስተር ዩናይትድ፣ ሌሲስተር ሲቲ፣ ቸልሲ፣ አርሰናልና ዌስት ሀም በእኩል 8 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው ከ4-9 ያሉትን ደረጃዎች ይዘዋል፡፡

ኤሲ ሚላን አዲስ የፀረ-ዘረኝነት አሠራር ይፋ ሊያደርግ ነው፤ አሠራሩ ይፋ የሚደረገው ከ‹ኢንተር ደርቢ› ጨዋታ አስቀድሞ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
ኢንተር ሚላን ‹‹የፀረ-ዘረኝነት ተከላካይ ግብረ ኃይል›› ሊያቋቁም መሆኑን በዋና ሥራ አስፈጻሚው በኩል ነው ያስታወቀው፡፡ የጣልያኑ የእግር ኳስ ቡድን ይህን ያለው በቅርቡ የዘረኝነት ትንኮሳዎች እየተበራከቱ መምጣታቸውን ተከትሎ ነው፡፡

ከሳምንታት በፊት ሮሜሉ ሉካኮ የፍጹም ቅጣት ምት በሚመታበት ወቅት የካግላሪ ደጋፊዎች በዘረኝነት መዝሙር ማሸማቀቃቸውን ያስታወሰው የሚላን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ‹‹የጣልያን እግር ኳስ መንቃት አለበት›› ሲል ተናግሯል፡፡

ግብረ ኃይሉ ግንዛቤ የሚያስጨብጡ መርሀ ግብሮችን ያዘጋጃል፣ በማኅበራዊ ሜዲያዎችና ስታዲዮሞች የሚተላለፉ የዘረኝነት ትንኮሳዎችን ይከታተላል ያርማል፡፡

ቡድኑ የፀረ ዘረኝነት አሠራር ለመዘርጋት እንቅስቃሴ ከጀመረ የቆየ ቢሆንም የቅርብ ጊዜ ሁኔታዎች በፍጥነት ወደ ተግባር እንዲገባ እንዳስገደዱት ታውቋል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ
በአብርሃም በዕውቀት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here