በራያ ግንባር የሚገኙ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣የአማራ ልዩ ኃይል እና የአማራ ሚሊሻ አባላት ድጋፍ አደረጉ፡፡

783
ነጭመደበኛ
ነጭመደበኛ
በራያ ግንባር የሚገኙ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣የአማራ ልዩ ኃይል እና የአማራ ሚሊሻ አባላት ድጋፍ አደረጉ፡፡
ባሕር ዳር፡ ኅዳር 11/2013 ዓ.ም (አብመድ) የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ኅዳር 9 /2013 ዓ.ም ባስተላለፈው የዜና ዘገባ በራያ ዋጃ የትህነግ ከሐዲ ቡድን አመራሮች ሲያደርሱት የነበረው የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ ግድያና አፈና በተመለከተ መዘገባችን ይታወሳል፡፡
በዘገባችንም የህገወጡ ትህነግ ቡድን የግፍ ጽዋ ከቀመሱት የአራት ልጆች እናት ከሆኑት ወ/ሮ አበባ ጌጡ እና ሌሎች ተበዳይ ወገኖች ጋር ቆይታ አድርገን ነበር፡፡
የወ/ሮ አበባ ባለቤት ሀገራዊ የፖለቲካ ለውጥ ሂደትን ሲደግፉ ለታሰሩ ጓደኞቻቸው ድምጽ ለመሆን ሰላማዊ ሰልፍ በመሳተፋቸው ብቻ በህገወጡ ትህነግ በግፍ ተገድለዋል፡፡
ለልጆቻቸውና ለእርሳቸው ህይወት መሰረት የሆኑትን ባለቤታቸውን ማጣታቸው አሁን ላይ አስቸጋሪ ህይወትን እንዲመሩ እንደዳረጋቸው መግለፃቸውን አስመለክተን ዘግበናል፡፡
ሁሌም ከራሱ አልፎ ለሌሎች የሚኖረው የመከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ አባላት ዛሬም ሌላ ህዝባዊ ወገንተኝነታቸውን በተግባር አስመስክረዋል፡፡
ካለው ላይ ቆርሶ የሚመግበው ብሎም ህዝብና ሃገርን ከራሱ በፊት የሚያስቀድመው ሰራዊት ለእኒህ እናት አለሁሎዎት ብሏቸዋል፡፡
በራያ ግንባር የሚገኙ የሃገር መከላከያ ሰራዊት፣ የልዩ ኃይልና የሚሊሻ አባላት 2 ሰንጋ በሬ እና 5 በግና ፍየል ለወ/ሮ አበባ በሌተናንት ኮሎኔል መንገሻ አባተ ተበርክቶላቸዋል።
ወ/ሮ አበባ ጌጡም ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋነቸውን ገልፀው ሰራዊቱ ዘመቻውን በድል እንዲያጠናቅቅ እናታዊ ምርቃታቸውን ለግሰዋል፡፡
መረጃውን ከቆቦ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ነው ያገኘነው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here