“በወልቃይት ጠገዴ በኩል መተላለፊያ ኮሪደር ይከፈት የሚለው ግፊት ተቀባይነት የለውም” አቶ ምትኩ ካሳ

0
177
“በወልቃይት ጠገዴ በኩል መተላለፊያ ኮሪደር ይከፈት የሚለው ግፊት ተቀባይነት የለውም” አቶ ምትኩ ካሳ
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 27/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍ ለሚሹ ተረጂዎች እርዳታ ለማቅረብ በሚል አንዳንድ ምዕራባዊያንና ተቋሞቻቸው በወልቃይት ጠገዴ በኩል መተላለፊያ ኮሪደር ይከፈት የሚለው ግፊታቸው ተቀባይነት እንደሌለው የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ አስታወቁ።
እርዳታ አቅርቦቶች በፌዴራል መንግሥትና በአፋር ክልል ከፍተኛ ጥረት ለትግራይ ሕዝብ እየደረሰ መሆኑንም ነው ኮሚሽነሩ ያስታወቁት።
አቶ ምትኩ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፣ መንግሥት ያሳለፈውን የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ ባለመቀበል በአማራ እና በአፋር ክልሎች ላይ ትንኮሳ እየፈጸመ ያለው አሸባሪው ትህነግ ለትግራይ ክልል ተረጂዎች የሚቀርብን እርዳታ የያዙ ከ170 በላይ ተሽከርካሪዎችን አግቶ በማቆየቱ በክልሉ ያሉ ተረጂዎች ለከፍተኛ አደጋ ተጋልጠዋል።
ይህንን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም አንዳንድ ምዕራባዊያን ሀገራትና ተቋሞቻቸው ከሱዳን ቀጥታ እርዳታ ለማስገባት በሚል በወልቃይት ጠገዴ በኩል መተላለፊያ ኮሪደር ይከፈት የሚል ጥያቄዎችን ማቅረባቸውን ጠቁመዋል።
አንዳንድ ምዕራባዊያን ሀገራትና ተቋሞቻቸው ይህንን ይበሉ እንጂ መንግሥት ለተረጂዎቹ እርዳታ ለማቅረብ የጅቡቲው መስመር በቂ መሆኑን በማሳወቅ ተጨማሪ ኮሪደር እንደማይከፈት ማሳወቁን በዚህም የጸና አቋም እንዳለው አስታውቀዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here