“በምርጫው የታየው ሰላማዊነት እና ስልጡን አካሄድ በድህረ ምርጫውም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት” የአዲስ አበባ ነዋሪዎች

0
38

“በምርጫው የታየው ሰላማዊነት እና ስልጡን አካሄድ በድህረ ምርጫውም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት” የአዲስ አበባ ነዋሪዎች
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 15/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን መርጠዋል። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ
የምርጫ ጣቢያዎች ጊዜያዊ የምርጫ ውጤት እየተገለጸ ነው።
በከተማ አስተዳደሩ በትላንትናው እለት እስከ ምሽት ሦስት ሰዓት የተካሄደው ምርጫ ከተጠናቀቀ በኋላ ሌሊት ላይ እና እስከ ዛሬ
ረፋድ ድረስ ቆጠራው ሲከወን ቆይቶ በጣቢያ ደረጃ ጊዜያዊ ውጤት ይፋ እየሆኑ ነው። ከማለዳው ጀምሮም የከተማዋ ነዋሪዎች
በምርጫ ጣቢያዎች ላይ እየተገኙ የተለጠፈውን ጊዜያዊ ውጤት ድምጽ በሰጡባቸው የምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት
እየተመለከቱ መሆኑን አሚኮ ቃኝቷል።
የአሚኮ ዘጋቢ ጋሻው ፈንታሁን በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ምርጫ ጣቢያ 3 እና 9 ላይ ጊዜያዊ የምርጫ ውጤቱን
ሲመለከቱ ያገኛቸው የአካባቢው ነዋሪ አቶ አብርሃም ክፍሌ በምርጫው የታየው ሰላማዊነት እና ስልጡን አካሄድ በድህረ
ምርጫውም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡
ሌላዋ ነዋሪ ወይዘሮ አበበች አምባቸው ጥቅል ሀገራዊ ውጤቱ ምንም ይሁን ምን ሀገርና ሕዝብን ማስቀደም ይገባል ነው ያሉት።
የሕዝብ ድምጽ ውጤት በጸጋ መቀበል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ምርጫ አንዱ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አካል እንጅ የሁሉም ነገር መወሰኛ ባለመሆኑ ሕዝቡ ሀገሩን አክብሮ ከማለዳ እስከ
ምሽት ድምጹን ሰጥቷል ፤ ፓርቲዎችም የተሰጠውን የድምጽ ውጤትም በማክበር ለሀገርና ለሕዝብ ያላቸውን አክብሮት በተግባር
እንዲያሳዩም የከተማዋ ነዋሪዎች ጠይቀዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here