ደሴ:መጋቢት 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ለቡና እና አትክልት ልማት ምቹ ሁኔታ ቢኖረውም በሚፈለገው መጠን አለመልማቱን ከክልሉ ግብርና ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ቢሮው በቀጣይ ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ ያለመ ውይይት ከባለድርሻ አካላት ጋር በደሴ ከተማ አካሂዷል።
የውይይቱ ተሳታፊዎችም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቆላ እና ደጋ ፍራፍሬ ላይ የተጀመሩ ሥራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በቀጣይም ሰፊ ዝግጅት በማድረግ የአትክልት እና ፍራፍሬ ልማት ላይ በትኩረት ለመሥራት መዘጋጀታቸውን ነው ባለሙያዎቹ የተናገሩት።
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ቃልኪዳን ሽፈራው ክልሉ በቡና አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ምቹ ቢሆንም በበቂ ሁኔታ መጠቀም አለመቻሉን ገልጸዋል።
በመጪው ክረምት ከ19 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን ለማልማት መታቀዱን የገለጹት ምክትል ኀላፊው ለዚህም አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል። ከዚህ ውስጥ ከ11 ሚሊዮን በላይ የቡና ችግኝ እንደሚለማ ጠቅሰዋል። በቀጣይ ወራትም ዕቅዱን ለማሳካት በትኩረት መሥራት እንደሚገባ ነው የገለጹት
ዘጋቢ፦ ተመስገን አሰፋ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!