በመጀመሪያቸው መጨረሻቸው — ቅራቅር

0
299
በመጀመሪያቸው መጨረሻቸው — ቅራቅር
ባሕር ዳር ፡ የካቲት 11/2013 ዓ.ም (አብመድ) የደደቢት ሽፍቶች፣ የዚያ ዘመን ነፃ አውጪዎች፣ የኢትዮጵያ አድራጊ ፈጣሪዎች፣ የቤተ መንግሥት ፈላሾች፣ የመቀሌ አድራጊ ፈጣሪዎች፣ ለዳግም ስልጣን ጥመኞች፣ የሀገርን ደጀን ተንኳሾች፣ የአማራ ሕዝብ ጠላቶች ለዳግም ስልጣን ጥም ጥቅምት 24 ከዓመታት በፊት የመጡበትን አፈ ሙዝ አነሱ። በመከላከያ እና በአማራ ክልል ላይ ተኮሱ፣ ዳግም ላይመለሱ፣ ከወደቁበት ላይነሱ በተባባረ ክንድ ተደመሰሱ።
የሀገር መካላከያ ሠራዊትን ከጀርባው ወጉት፣ የአጎረሰውን እጁን ነከሱት፣ ወርቅ ሰጥቷቸው ጠጠር መለሱለት፣ በዚያ አልበቃቸውም የአማራን ልዩ ኃይል በቅራቅር ተነኮሱ። ምኞታቸው የጀግኖችን ምድር ጎንደርን አልፈው ፈልሰው ወደ ወጡበት ቤተመንግሥት መገስገስ ነበር። ይህ ግን አልሆነም። በሌሊት ጀምረው፣ በሌሊት ተመክተው፣ በሌሊት ተመትተው፣ በሌሊት ተረትተው፣ በለኮሱት እሳት እየተለበለቡ፣ ወደ ኋላ አፈገፈጉ፣ ፈረጠጡ፣ “አትንኩን ብለናል ከነኩን ወዲያማ ማንስ ያቆመናል” የሚለው የአማራ ልዩ ኋይል እና ሚሊሻ ለተወገው ደጀኑ ደረሰለት። ጠላቱንም ደመሰሰለት።
ለዳግም ስልጣን ምኞት ጥቅምት 24 ምሽት የጀመሩትን መሠረት በማድረግ ለተፈፀመው የህግ ማስከበር ጀብዱ የሚዘክር “ዝክረ ጥቅምት 24” በጠገዴ ቅራቅር ተደርጓል። በየካቲት 11 በመጀመሪያቸው ቀን የመጨረሻው ቀን እየተፈፀመም ነው። በዝክረ ጥቅምት 24 ቀን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር፣ የክልሉ ምክር ቤት አፈጉባኤ ወርቀሰሙ ማሞ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ፈንታ ማንደፍሮ፣ የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አብርሃም አለኸኝን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የከተማዋ ነዋሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ