በመስኖ ልማት ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት እና ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ለማድረግ የክልሉ መንግሥት ቁርጠኛ መሆኑን የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ገለጹ፡፡

0
52
ባሕር ዳር፡ ሕዳር 26/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መሥተዳድሩ በአማራ ክልል በግብርናው ዘርፍ ከተሰማሩ ባለሃብቶች ጋር ለመስኖ ስንዴ ልማት በተመረጡ መሬቶች ላይ ወደ ሥራ እንዲገቡ የሚያስችል የምክክር መድረክ ዛሬ አካሂደዋል፡፡
በመስኖ ልማት ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት እና ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ለማድረግ የክልሉ መንግሥት ቁርጠኛ መሆኑን የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ገልጸዋል፡፡
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በፈጸመው ወረራ የወደመውን የሰብል ምርት ለማካካስም ኾነ የኅብረተሰቡን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ በግብርናው ዘርፍ የተሰማሩ ባለሃብቶች ከምንግዜውም በላይ በሙሉ አቅማቸው ወደሥራ እንዲገቡ ርእሰ መሥተዳድሩ ጥሪ አቅርቀዋል።
በክልሉ መልማት የሚችል የመስኖ መሬት በምንም ምክንያት ጾም ማደር እንደሌለበት የገለጹት ርእሰ መሥተዳድሩ በዘርፉ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በየደረጃው ያለው የመንግሥት መዋቅር እንደሚፈታም ተናግረዋል፡፡
በኢንቨስትመንት የወሰደውን መሬት ያላለማ ባለሃብት መሬቱ ተወስዶ ማልማት ለሚችል ባለሃብት እንደሚሸጋገርም ተጠቁሟል።
በክልሉ አንጻራዊ ሰላም ባለባቸው አካባቢዎች 34 ሺህ ሄክታር መሬት በዘርፉ በተሰማሩ 20 ባለሃብቶች በመስኖ ስንዴ ለማልማት መታቀዱን ከቢሮው የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ዘጋቢ፡- ባለ ዓለምዬ
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation