በሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የታሪፍ ማሻሻያ መደረጉ ተገለፀ

561

ባሕር ዳር: ጥር 01/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉን ተከትሎ ከጥር 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የታሪፍ ማሻሻያ ማድረጉን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አሰታወቀ።

ማሻሻያው በጀረጃ 1፣ ደረጃ 2 እና በደረጃ 3 ተሸከርካሪዎች ላይ ተግባራዊ ይደረጋል። ማሻሻያው በአስፋልት እና በጠጠር መንገድ ላይ የሚኖራቸውን እንቅስቃሴ ታሳቢ ያደረገ ነው ተብሏል።

የሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አሽከርካሪዎችና ረዳቶች በተቀመጠው ታሪፍ ብቻ በማስከፈል አገልግሎት እንዲሰጡ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።

ህብረተሰቡም ይህን አውቆ ከታሪፍ በላይ የሚጠይቁ አካላትን ለትራንስፖርት ተቆጣጣሪዎች እንዲሁም በየደረጃው ለሚገኙ የህግ አስከባሪ አካላት ሪፖርት በማድረግ ህግ የማስከበሩ አካል እንዲሆን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ጠይቋል። ዘገባው የኢፕድ ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!