“ስሟን ለማደስ እጅግ ከፍተኛውን ጀግንነትና ለማሰብ የሚከብደውን ብቃት ስላሳያችሁ ኢትዮጵያ አብዝታ ታከብራችኋለች” የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

0
183

ጥር 01/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በመከላከያ ሚኒስቴር ዋና መሥሪያ ቤት ምረቃ ላይ የተገኙት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በሕግ ማስከበር እና የኅልውና ዘመቻው በመከላከያ ኃይሉ በሳል አመራር የሰጡ እና ጀብዱ ለፈጸሙ መኮንኖች የሀገሪቱን ከፍተኛ ብሔራዊ ሚዳሊያ ሸልመዋል።

ባለፉት የጦርነት ወራት ፈተናን ተቋቁመው፣ መከራን ታግሰው እና ጀግንነትን ተላብሰው የተዋጉ እና ያዋጉ አባላት መኖራቸውን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ስሟን ለማደስ እጅግ ከፍተኛውን ጀግንነትና ለማሰብ የሚከብደውን ብቃት ስላሳያችሁ ኢትዮጵያ አብዝታ ታከብራችኋለች” ብለዋል።

ላሸነፈ ሽልማት ለተሸነፈ ምሕረት መሥጠት የታሪካችን ክፋይና ኢትዮጵያ የሚለው ስም ብያኔ አካል ሆኖ የቆየ ነው ብለዋል።

ጠላቶቻችን በለመዱት ሳይሆን በተለየ መንገድ ኢትዮጵያን ማጽናት እንፈልጋለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መከላከያ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የሚመጥን መልኩ የማደራጀቱ ሂደት ይቀጥላል ነው ያሉት።

የኢትዮጽያ ጠላቶች ጥቂት ግለሰቦች አይደሉም፤ የኢትዮጽያ የኅልውና አደጋም ገና አልተወገደም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚገጥመን ጦርነት መልከ ብዙ ነውና ዘርፈ ብዙ ዝግጅት ይጠይቃል ብለዋል።

ዘጋቢ፦ ታዘብ አራጋው

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/