ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዥዩዋን ጋር ተወያዩ።

49

ባሕር ዳር: ግንቦት 17/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በዛሬው እለት በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዥዩዋን ጋር በቢሯቸው ተወያይተዋል። ርእሰ መሥተዳድሩ ዶክተር ይልቃል ከፋለ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዥዩዋን ጋር ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ እና ቻይና ረጅም ዘመናት የዘለቀ ጠንካራ የትብብር ግንኙነት ያላቸው ሀገራት ናቸው ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ።

በአማራ ክልልም በትምህርትና ሥልጠና፣ በቴክኖሎጂ ትውውቅና በተለያዩ የትብብር መስኮች በጋራ ለመሥራት የጀመርነውን ግንኙነቶች ይበልጥ አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል። ክልላችን የበርካታ ጸጋዎች ባለቤት ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፍ ኢንቨስት ማድረግ ለሚፈልጉ የቻይና ባለሐብቶች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉም ገልጸዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!