ርእሰ መሥተዳድሩ በሰሜን ሸዋ ዞን የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ የመስኖ ልማት እንቅስቃሴን ጎበኙ፡፡

0
333

የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ በሰሜን ሸዋ ዞን የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ የመስኖ ልማት እንቅስቃሴን ዛሬ ሚያዝያ 24/2012 ዓ.ም ጎብኝተዋል።

በወረዳው በመጀመሪያ ዙር መስኖ 851 ሄክታር መሬት መልማቱን ከግብርና ጽህፈት ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ ከዚህም 1 መቶ 91 ሺህ ኩንታል ምርት እንደተገኘ ነው ጽህፈት ቤቱ የገለጸው፡፡

የመስኖ ልማቱ 4 ሺህ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ እንዳደረገም ታውቋል፡፡ የርእሰ መሥተዳድሩ የመስክ ምልከታ ዓላማ ደግሞ ከግብዓት አቅርቦትና ከገበያ ትስስር ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመፍታት እንደሆነ ነው የተገለጸው፡፡

ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ ባሳለፍነው ሳምንት በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር፣ በምሥራቅ እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች እየተከናወኑ ያሉ የመስኖ ልማት ተግባራትን መጎብኘታቸውና ከገበያ ትስስር ጋር በተያዘ ለተነሱ ችግሮች መፍትሄ እንደሚፈለግላቸው መናገራቸውንም አብመድ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

ዘጋቢ፡- ስማቸው እሸቴ